You are currently viewing ኮቪድ-19ን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የመመርመር ውጥን
ኮቪድ-19ን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የመመርመር ውጥን

ኮቪድ-19ን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የመመርመር ውጥን

ዓለም በተለያዩ ጊዜያት አብዮቶችን አስተናግዳለች፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና የመረጃ አብዮቶች ይጠቀሳሉ፡፡ አሁን ደግሞ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የሰዎችን ሥራ የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም ላይ ተደርሷል፡፡ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተለያዩ ዘርፎችን ለማዘመን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይታመናል፡፡ በሰው ጉልበት የሚከናወኑ ተግባራትን በቴክኖሎጂ በመደገፍ የገንዘብ፣ የጊዜና የጉልበት ብክነትን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ መሆኑ ይታመናል፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ በእርሻ፣ በኢንዱስትሪ፣ በመረጃና በሌሎች ቴክኖሎጂውን ቀስ በቀስ እየተተገበረ ቢሆንም፣ በታሰበለት ልክ መራመድ እንዳልተቻለ የግብርናው ዘርፍ ማሳያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን በበሬና በፈረስ የሚያርስ አርሶ አደር መኖር ከፊል ለውጥ ከመታየት ውጪ ቴክኖሎጂው ሙሉ ለሙሉ እየተተገበረ እንዳልሆነ ማሳያ ነው፡፡ በተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ዘርፈ ብዙ ቴክኖሎጂዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኘው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተጠቃሽ ነው፡፡ በኢንስቲትዩቱ መምህር የሆኑት ጀርሚያ ባይሳ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በመጠቀም የተለያዩ ሥራዎችን ሠርተዋል፡፡ ሔለን ተስፋዬ አነጋግራቸዋለች፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ (አሁን ላይ እየመጡ ያሉ) በሚታገዙ ሥራዎች ዕገዛ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡ በዩኒቨርሲቲው ብዙ ሥራዎችን ሊያቀሉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ላይ እንገኛለን፡፡ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በዓለማችን ከተከሰተ ጊዜ አንስቶ በቴክኖሎጂ እንቅስቃሴዎችን ለማገዝ ጥረት አድርገናል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ምላሽ አሰጣጥ ካለው የተለያዩ ሪሶርሶች እጥረት አንፃር ችግሩን ያቀላል ያልነውን ቴክኖሎጂ ይዘን ብቅ ብለናል፡፡ ለምሳሌ የመመርመር አቅምን ለማሳደግ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ሞክረናል፡፡ የመጀመርያ ሥራችን የነበረው በአርቴፊሸል ኢንተለጀንስ (ማሽን ለርኒንግ) በመጠቀም፣ አሁን ደግሞ ለየት ያለውን ቨርዥን (ዲፕለርኒንግ) በመጠቀም መረጃ ለመሰብሰብ ተጠቅመንበታል፡፡ አንድ የጤና ባለሙያ ዶክተር፣ ነርስና ሌሎችም የሚያውቀውን ዕውቀት በዲፕ ለርኒንግ ማሽን ይሰጥና እንደ ሙያው ሥራዎችን እንዲሠራ የሚደረግበት ዘዴ ነው፡፡ ለምሳሌ በምርመራ ሒደት ቫይረሱ ያለበትንና የሌለበትን የመለየት ሥራ በማሽን ለርኒንግ ዲቨሎፕመንት ሞዴል መረጃው ከተሰጠው በኋላ ቫይረሱ ያለበትንና የሌለበትን ሰው መለየት ይቻላል ማለት ነው፡፡ እኛ የሠራነው ሲቲ እስካን ምሥልን በመጠቀም ነው፡፡ እስካሁን የተደረጉ ምሥሎች ላይ ማሽኑ መረጃ በተሰጠው መሠረት በቫይረሱ የተያዙና ያልተያዙ በማለት ይለያል፡፡ ከምሥሉ ከተገኘ ደግሞ የመመርመር አቅሙን መጨመርና በቀላሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መለየት የሚቻልበትን መንገድ አሳድገናል፡፡ 

ይህ ሥራ የተሠራው መጀመርያ በቻይናዎች ነው፡፡ የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከእነሱ ነበር፡፡ አሁን ላይ ከጅማ ኮሮና ቫይረስ ሴንተር የተገኘውን መረጃ እየጨመርን ተዓማኒነቱን ከፍ እያደረግን እንገኛለን እንጂ መጀመርያ ተግባራዊ ያደረጉት ቻይናውያን ናቸው፡፡ እኛም ስንጀምር የተጠቀምነው ዳታ የእነሱን ነበር፡፡ እኛ ያሰብነው የኮሮና ቫይረስ መመርመርያ እጥረት ባለበት ቦታዎች ላይ እንዲያግዝ ለማድረግ ነው፡፡ በዋናነት ግን በምሥል ብቻ የሚሠራ ነው፡፡ አሁን እየሠራን ያለነው ከሌሎች በሽታዎች የሚለዩበትንና ሌሎችን በመጨመር በይበልጥ እያሳደግነው እንገኛለን፡፡ ከዚህ በፊት የነበረው ልምድ ከምሥሉ ላይ ያለውን በማንበብ ብቻ ፖዘቲቭና ኔጋቲቭ ብሎ የሚለይ ነበር፡፡ አሁን ላይ ግን የተለያዩ ቫይረሱ የሚለዩበትን መረጃ መጨመር፣ ከዚህ የሚያመልጡት በሌላ ዘዴ ናሙና ወስዶ መረጃ ማሳወቅ ነው፡፡ በመረጃው በየትኛው ዘዴ እንደሚወሰድ ከታወቀ በኋላ በኮምፒዩተር ቪዥን፣ በዳታ ማይኒንግ ወይም በኢሜጂንግ በሚቻለው መንገድ እየተሠራ ይሄዳል፡፡  ከሐሳቡ እንኳን ስንነሳ የሳንባ በሽታ የሚለየው በዚሁ መንገድ ነበር፡፡ ተመሳሳይ ባህሪያት ስላለው ነው፡፡ ማሽን ዲፕ ለርኒንግ በጣም ባስተማርሻቸውና ባሳወቅሻቸው ቁጥር ሰዎች ያሉትን ነገሮች ማየት ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የእኛ ሥራ ማሽኑን እንድንተማመንበት የሚያደርገን ብዙ መረጃ፣ ሥልጠናና የተለያዩ ኬዞችን በማስተማር በሚፈለገው መጠን የሚሠራ ይሆናል፡፡

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚተዳደረው ወይም ኑሮው የተመሠረተው በግብርና ላይ ነው፡፡ ሰፊው የውጭ ምንዛሪና ዕምቅ ሀብት የሚገኘው ከቡና ምርት ነው፡፡ እንደሚታወቀው ቡና በጅማና አካባቢዋ በይበልጥ የሚታወቀው በዚሁ ዕፀዋት ነው፡፡ በኢትዮጵና በኬንያ የተሠራ ጥናት 57 በመቶ የሚሆነው ምርት በቡና በሽታ ምክንያት የሚጠፋ መሆኑን ያሳያል፡፡ ‹ኮፊ ሊቮረስት› የሚባለው የቡና በሽታ ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስ ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህን በሽታ ቀደም ብሎ መለየት ለችግሩ መፍትሔ ማበጀት ነው፡፡ በዋናነት በበሽታው ከመያዛቸው በፊት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንት አማካይነት በሽታው ሥር ሳይሰድ የሚሠሩ ናቸው፡፡ ምርታማነቱን ከመጉዳቱ በፊት ልክ እንደ ሰዎች በሽታው ሥር ሳይሰድ የሚሠራ የቴክኖሎጂ ዓይነት ነው፡፡ እኛ የሠራነው በሽታው ሥር ሳይሰድ የሚጠቁም ከመሆኑ በበለጠ፣ በሽታውን ማስቆም የሚችሉ ዘዴዎች በባህላዊና በዘመናዊ ሕክምናዎች ምክሮችን የሚጠቁም ነው፡፡ በዚህኛው ሥራ እ.ኤ.አ. 2019 በግሪን ኢንሼቲቭ አግሪቴክ ከኢትዮጵያ አንደኛ ሆነናል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2020 ደግሞ ከሰባት የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ደቦ ኢንጂነሪንግ ተመርጧል፡፡ ደቦ ኢንጂነሪንግ ከአሥር ሌሎች አፍሪካ አገሮች ጋር የምርጦች ምርጥ ውድድር ቀጥሏል፡፡

በዚህ ላይ በሕዝብ ምርጫ አንደኛ ወጥቷል፡፡ ዘንድሮ 2021 (2013 ዓ.ም.) ኮቪድ-19 ኮንቬንሽን ፈንድ እንደ ሰብ ሰሃራ አወዳድሮ 2.5 ሚሊዮን ብር ተሸላሚ ሆነናል፡፡ አሁን የዚህኛው የሽልማት ሥርዓት በሒደት ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ወርልድ ሰሚት አፎርድ ላይ ከ80 አገሮች 90 በመቶዎቹ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ናቸው፡፡ ከዚህ ውስጥ ‹‹The Best and Most Digital Innovative from the Country›› በሚል ውድድር ምርጥ 40ዎቹ ውስጥ ገብተን ነበር፡፡ በአፍሪካ ዊክ ኢኖቬንሽን በጣም ጠንካራ የሚባሉ ተወዳዳሪ ያሉባቸው ባለሙያዎች ባሉበት እየተወዳደርን እንገኛለን፡፡ አሁን ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመምህርነት በተጨማሪ ከጓደኛዬ ጋር በመሆን ‹‹ደቦ ኢንጂነሪንግ›› የሚባል ስታርት አፕ ካምፓኒ መሥርተዋል፡፡ ይህም በዋናነት የግብርና ዘርፍን የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎችን ከግብርና፣ ከማቲማቲክስ፣ ከኮምፒዩተርና ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንት ባለሙያዎች ጋር የምንሠራ ይሆናል፡፡ በጤና ዘርፉም እንዲሁ የተለያዩ ባለሙያዎች ስብጥር የሚሠራ ይሆናል፡፡ አሁንም በኮሮና ቫይረስ መመርመር የሚችለው በሲቲስካን ምሥል የተለያዩ መረጃዎች በማሰባሰብ ለማሳደግ ጥረት እያደረግን እንገኛለን፡፡

subscription image

The latest news from the company straight to your inbox.

Join 12,000+ subscribers for exclusive access to our monthly newsletter!

Leave a Reply